Entries by

መስቀል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::   ከጌታችንና ከአምላካችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በፊት መስቀል የመቅጫ መሣሪያ ነበር። ሰውን በመስቀል ላይ መቅጣት የተጀመረውም በፋርስ ነው። ፋርስ የዛሬዋ ኢራን ናት። የፋርስ ሰዎች “ኦርሙዝድ” የተባለ “የመሬት አምላክ” ያመልኩ ነበር። ከዚህም የተነሣ “ወንጀለኛው ቅጣቱን በመሬት ላይ የተቀበለ እንደሆነ አምላካችን ይረክሳል፤” ብለው ስለሚያምኑ ወንጀለኛውን ከመሬት ከፍ አድርገው በመስቀል […]

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው?

፩. ሥርዓት ምንድን ነው?   ሥርዓት “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ስንልም የቤተ ክርስቲያን ዕቅድ፣ የቤተ ክርስቲያን አሠራር መርሐ ግብር ወይንም ደንብ ማለታችን ነው።   ሥርዓት የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፦ ·        ሥራን ወጥ በሆነ መልኩ ለመፈጸም ማንኛውንም ነገር ወጥና ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመሥራት ከየት ተጀምሮ […]

በኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት በተፈጸመው ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ለተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጐዱት ካህናትና ምእመናንን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው የድጋፍ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ በኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት በተፈጸመው ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ለተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጐዱት ካህናትና ምእመናንን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው የድጋፍ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ፡፡ በተከሰተው ግርግርና ግጭት አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው፤ ካህናትና ምእመናን መገደላቸው፤ ንዋየ ቅድሳት መዘረፋቸውና የአብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮችና ምእመናን ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙኅን የተገለጸ ሲሆን እስካሁን የተደረገው ድጋፍ […]

በአሜሪካ ማእከል የካሮላይና ግንኙነት ጣቢያ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አስመረቀ

በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል ካሮላይና ግንኙነት ጣቢያ የሚገኘው የአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ለሁለት ወራት የክረምት ትምህርት ያስተማራቸውን ሰባ ስድስት (፸፮) ተማሪዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት በመስጠት የክረምቱን መርሃ ግብር ነሐሴ ፲፱ ቀን ፳፻፲ ዓም አጠናቋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በሻርለት ኖርዝ ካሮላይና የመካነ ብርሃን ቅድሥት ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መሪጌታ ሰናይ ተገኝተው […]