Entries by

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል አዘጋጅነት የባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር ጉባኤ ተደረገ

የኢ/ኦ/ተ ቤ/ክርስቲያንን አገልግሎት ለሕፃናት ፣ አዳጊዎችና ወጣቶች እንዲሁም ለተጠመቁና ለሚጠመቁ የውጭ አገር ዜጎች ለማድረስና ለማስፋፋት ከሚያገለግሉ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር ጉባኤ ተደረገ።   በጉባኤውም በቀሲስ ሰይፈሥላሴ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ካህናት እንዲሁም የጉባኤው ተሳታፊዎች የአገልግሎት ማኅበራት የአገልግሎት ልምዳቸውን ለጉባኤው አካፍለዋል። በመቀጠልም ህጻናትን፣ አዳጊዎችንና ወጣቶችን እንዲሁም የውጭ አገር ዜጎችን ትምህርተ ሃይማኖት ለማስተማርና […]

በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል አስተባባሪነት በተያዘው በጀት ዓመት ከተለያዩ አጥቢያዎች ለተወከሉ 59 የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በተለያዩ 3 ቦታዎች በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተተኪ መምህራን ሥልጠና ተሰጠ።

    በዋና ክፍሉ ሪፖርት እንደተገለጸው የሥልጠናው ዓላማ ሠልጣኞቹ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ወንጌልን ሊያዳርሱ የሚችሉበትን ዕውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ ለማገዝ ሲኾን ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ)፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ የቤተክርስቲያን ታሪክና የስብከት ዘዴ በሥልጠናው የተካተቱ የትምህርት ዓይነቶች ናቸው፡፡ ሥልጠናዎቹ የተሰጡትም ከየካቲት 8 እስከ 10 2011 ዓ.ም በዲሲና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል፣ […]

በዓለ ግዝረት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በዓለ ግዝረት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ ዓለም በህሊና ያሰበውን፤ ድኅረ ዓለም በነቢያት ያናገረውን ለመፈጸም ሰው ሆነ፣ ሥጋ ለበሰ፤ ሕግ ጠባያዊን ሕግ መጽሐፋዊን እየፈጸመ በጥቂቱ አደገ። ሕግ ጠባያዊ፤ አበ፣ እመ ማለት፣ ለዘመድ መታዘዝ፣ በየጥቂቱ ማደግ ነው። “ወልህቀ በበኅቅ እንዘይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ ወለይእቲ እሙ” እንዲል። ሕግ መጽሐፋዊ በስምንት ቀን […]

በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ

በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ                                 ቀሲስ ሳሙኤል ተስፋዬ በፈቃደ አቡሁ ወረደ፣ኀበ ማርያም ተአንገደ፤ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ። በጎለ እንስሳ ተወድየ፣ አምኃ ንግሡ ተወፈየ፤ ወከመ ሕጻናት በከየ፣ እንዘ ይስእል እምአጥባተ እሙ ሲሳየ። በአባቱ ፈቃድ ወረደ፣ በማርያም ዘንድ፣ እንግዳ ሆነ፣ እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ። በእንስሳት በረት ተጨመረ፣ የንግሡንም እጅ መንሻ፡ ተቀበለ፣ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕጻናት […]

ሰንበት ዘብርሃን

ሰንበት ዘብርሃን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ነአምን ክልኤተ ልደታተ እንዳሉ አባቶቻችን በሃይማኖተ አበው፤ ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት፣ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደ፣ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ አካላዊ ቃል ፤ ድኀረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት፣ መለወጥ ሳያገኛት ዘር ምክንያት ሳይሆን፣ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነ […]