• እንኳን በደኅና መጡ !

የአብይ ጾም ሳምንታት

ሰሙነ ሕማማት (Passion week: Latin passio -suffering)

በኩረ ፍሥሐ ቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መመስከር እንዲገባ “ይደልዎነ ንአምን ከመ ቦቱ ለወልደ እግዚአብሔር ክልኤቱ ልደታት ቀዳማዊ ልደቱ እም እግዚአብሔር አብ እምቅድመ ኩሉ መዋዕል ወዳግማዊ ልደቱ እም እግእዝትነ ቅድስት ድንግል ማርያም በደኃራዊ መዋዕል” ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፮ ክፍል ፭ ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት አካል ዘእምአካል ባህሪ ዘእምባህሪ የተወለደ ተቀዳሚ […]

የካህናት ኃላፊነትና የምእመናን ድርሻ

ጌታችንና መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲ ላይ “ኖላዊ ኄር ቸር እረኛ እኔ ነኝ” ሲል አስተምሯል። በዚህ የወንጌል ክፍል ጌታችን ስለአመጣጡ – ትንቢት ተነገሮለት፣ ሱባዔ ተቆጥሮለት፣ የባህርይ አባቱ እግዚአብሔር አብ መስክሮለት የመጣ መሆኑን፣ የመጣውም ለምኅረትና ለቤዛነት መሆኑን ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለፍጥረቱ /ለበጎች/ ምእመን የሚራራ ቸር ጠባቂ መሆኑን አስተምሮበታል። ትምህርቱ ጥልቅ መንፈሳዊ መልእክት ያለውና […]

ስለምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? /ኢሳ. ፶፰፥፫/

በቀሲስ ስንታየሁ አባተ በኢሳያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተናገሩት ቃል ነው። እስራኤላውያን የሚጾሟቸው ብዙ አጽዋማት ነበሯቸው። ለምሳሌ ያህልም ብናይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን ይጾሙ እንደነበር በሉቃ. ፲፰፥፲፪ ላይ ያለው ቃል ያስረዳል። ማክሰኞና ሐሙስ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ ደብረ ሲና የወጣበትና ከዚያ የወረደበት ዕለት ለማሰብ እስራኤላውያን በሳምንት ሁለት ቀኖች ይጾሙ ነበር። በነቢዩ በዘካርያስ ትንቢትም ላይ […]

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል አዘጋጅነት የባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር ጉባኤ ተደረገ

የኢ/ኦ/ተ ቤ/ክርስቲያንን አገልግሎት ለሕፃናት ፣ አዳጊዎችና ወጣቶች እንዲሁም ለተጠመቁና ለሚጠመቁ የውጭ አገር ዜጎች ለማድረስና ለማስፋፋት ከሚያገለግሉ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር ጉባኤ ተደረገ።   በጉባኤውም በቀሲስ ሰይፈሥላሴ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ካህናት እንዲሁም የጉባኤው ተሳታፊዎች የአገልግሎት ማኅበራት የአገልግሎት ልምዳቸውን ለጉባኤው አካፍለዋል። በመቀጠልም ህጻናትን፣ አዳጊዎችንና ወጣቶችን እንዲሁም የውጭ አገር ዜጎችን ትምህርተ ሃይማኖት ለማስተማርና […]

በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል አስተባባሪነት በተያዘው በጀት ዓመት ከተለያዩ አጥቢያዎች ለተወከሉ 59 የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በተለያዩ 3 ቦታዎች በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተተኪ መምህራን ሥልጠና ተሰጠ።

    በዋና ክፍሉ ሪፖርት እንደተገለጸው የሥልጠናው ዓላማ ሠልጣኞቹ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ወንጌልን ሊያዳርሱ የሚችሉበትን ዕውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ ለማገዝ ሲኾን ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ)፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ የቤተክርስቲያን ታሪክና የስብከት ዘዴ በሥልጠናው የተካተቱ የትምህርት ዓይነቶች ናቸው፡፡ ሥልጠናዎቹ የተሰጡትም ከየካቲት 8 እስከ 10 2011 ዓ.ም በዲሲና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል፣ […]

በዓለ ግዝረት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በዓለ ግዝረት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ ዓለም በህሊና ያሰበውን፤ ድኅረ ዓለም በነቢያት ያናገረውን ለመፈጸም ሰው ሆነ፣ ሥጋ ለበሰ፤ ሕግ ጠባያዊን ሕግ መጽሐፋዊን እየፈጸመ በጥቂቱ አደገ። ሕግ ጠባያዊ፤ አበ፣ እመ ማለት፣ ለዘመድ መታዘዝ፣ በየጥቂቱ ማደግ ነው። “ወልህቀ በበኅቅ እንዘይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ ወለይእቲ እሙ” እንዲል። ሕግ መጽሐፋዊ በስምንት ቀን […]

መጽሐፈ ስንክሳር በድምጽ

የቀድሞውን ድረ ገጽ ከዚህ ያገኛሉ