Entries by

ቅድስት(የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

መልዕክታት የቅድስት ምንባብ 1(1ኛ ተሰ.4÷1-13) እንግዲህ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን እንመክራችሁማለን። በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና […]

ዘወረደ(የዐቢይ ጾም አንደኛ ሳምንት)

ጾሙን ሐዋርያት፣ ስያሜውንና የምስጋናውን ሥርዓት ቅዱስ ያሬድ አዘጋጅተዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ነቢያትን በንባብ፤ ሐዋርያትን በስብከት፤ ሊቃውንትን በትርጓሜ፤ መላእክትን በዜማ ይመስላቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ የመላእክትን የምስጋና ሥርዓት ወደ ምድር አምጥቷል፡፡ የነቢያትን ትንቢት፣ የሐዋርያትን ትምህርት በሚገባ ተርጒሞ፣ አብራርቶ፣ አመሥጥሮ አዘጋጅቶታል፡፡ ሐዋርያት ጾሙን ጾመው የጾም ሕግ ደንግገዋል፤ ቅዱስ ያሬድም ለጾሙ ስያሜ ሰጥቶ ምስጋና ከነሥርዓቱ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡ቤተ ክርስቲያናችንም የመጀመሪያው የዐቢይ ጾም […]

ማኅበረ ቅዱሳን በአትላንታ አስረኛውን የአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ከፈተ!

 ቀን ነሐሴ 14 ቀን 2011 ማኅበረ ቅዱሳን  በአትላንታ አስረኛውን የአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ከፈተ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን  በሰሜን አሜሪካ ማዕከል የአትላንታ ንዑስ ማዕከል አስረኛውን የአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ከፈተ፡፡   ከማዕከሉ የተተኪ ትውልድና ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ክፍል ሪፖርት መረዳት እንደተቻለው ፤ ማዕከሉ ከ፸፭ (ሰባ […]

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ

ከዓርብ ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ/ም እስከ ግንቦት 19 2011 ዓ/ም በኔቫዳ ግዛት ላስቬጋስ ከተማ “በሰላም ማሠሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ” ኤፌ 4፡3 በሚል ኃይለ ቃል ሲካሄድ የሰነበተው በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ፡፡” .. ” በአሜሪካ ማእከል ሥር ካሉት 12 ንኡሳን ማእከላትና 10 ግንኙነት ጣቢያዎች የመጡ የማኅበሩ አባላትና የአባላት ቤተሰቦች፣ ተጋባዥ […]

ምስክርነት

ዲያቆን ዮሴፍ በቀለ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፰ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገራቸው ቃል «በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፤ በሰማርያ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቼ ትሆኑኛላችሁ» የሚል ነው፡፡ ይሁዳ ኢየሩሳሌምን የሚያጠቃልል ግዛት ነው፤በኢየሩሳሌም የጌታችን ተአምር የተፈጸመበት፤ ብዙ ሰው ስለ እርሱ የሰማበትም ከተማ ነው፡፡ ከኢየሩሳሌም ይልቅ በይሁዳ ስለ ክርስቶስ የሚያውቁም የሚሰሙም ዝቅተኛ ናቸው፡፡ ሌላው ሰማርያ […]

ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ያሉት ዕለታት ስያሜያቸውና ታሪካዊ አመጣጣቸው

ዲያቆን ተመስገን ዘገየ ከትንሣኤ ሌሊት ፩ ሰዓት ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ያለው ሳምንት የፉሲካ ምሥጢር የተገለጠበት፤ ከግብፅ ወደ ምድረርስት ከሲኦል ወደ ገነት መሻገርን የሚያመላክት ሳምንት ነው። ለፉሲካ የሚታረደውም በግ ፉሲካ ይባላል (ዘዳ. ፲፮÷፪:፭÷፮)፤ ፉሲካ ማለት ደግሞ ማለፍ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትም ሳምንት የፉሲካ ሳምንት ነበር፤ (ሉቃ. ፳፪፥፲፬-፲፮፤ ዮሐ. ፲፰፥፴፰-፵)። እርሱም ንጹሕ የእግዚአብሔር በግ ሆኖ ደሙን […]