በኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት በተፈጸመው ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ለተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጐዱት ካህናትና ምእመናንን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው የድጋፍ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

በኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት በተፈጸመው ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ለተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጐዱት ካህናትና ምእመናንን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው የድጋፍ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ፡፡

በተከሰተው ግርግርና ግጭት አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው፤ ካህናትና ምእመናን መገደላቸው፤ ንዋየ ቅድሳት መዘረፋቸውና የአብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮችና ምእመናን ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙኅን የተገለጸ ሲሆን እስካሁን የተደረገው ድጋፍ ከደረሰው ጉዳት አንጻር ዝቅተኛ በመሆኑ ድጋፉ ላይ ምእመናን ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡

ከደረሰው ጉዳት አንጻር አብያተ ክርስቲያናቱን መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑና ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ወገኖችን በድጋፉ ላይ ለማካተት ይቻል ዘንድ ይህ የ’GoFundMe’ ገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገድ በብጹዕ አባታችን አቡነ ፋኑኤል የዋሺንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ ተከፍቶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ለዚህ ተግባር ሁሉም የወገን አለኝታነቱን ለመግለጽ በተግባር መገለጽ አለበት ተብሏል፡፡

ደጋፉን በማስተባበር ረገድ በሰሜን አሜሪካ የካህናት ማኀበር፣ በሰሜን አሜሪካ አኀጉረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ፣በማኀበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከልና በሰሜን አሜሪካ አኀጉረ ስብከት የማኀበረ በዓለወልድ ጥረት እያደረጉ ሲሆን በየአብያተ ክርስቲያናቱም የገንዘብ ማሰባሰቡ ጥረት ተጀምሯል::

የሚሰበሰበው ገንዘብ ተሰብስቦ እንዳለቀ ለዚህ አገልግሎት እንዲውል በኢትዮጵያ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ የሚያስገቡ መሆኑን አስቀድሞ መገለጹ የታወሳል፡፡ በመሆኑም አብያተ ክርስቲያናቱን ወደ ነበሩበት ይዞታ መመለስ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደረግ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡

የደረሰውን ጉዳትና ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የቀረበውን የድጋፍ ጥሪ በተመለከተ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማየት ይቻላል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=97bPK_5ofgU

ድጋፍ ለማድረግ ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም መለገስ ይቻላል::

https://www.gofundme.com/help-jigjiga-eotc-churches-and-victims