ዜና

በኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት በተፈጸመው ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ለተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጐዱት ካህናትና ምእመናንን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው የድጋፍ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

በኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት በተፈጸመው ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ለተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጐዱት ካህናትና ምእመናንን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው የድጋፍ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ፡፡

በተከሰተው ግርግርና ግጭት አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው፤ ካህናትና ምእመናን መገደላቸው፤ ንዋየ ቅድሳት መዘረፋቸውና የአብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮችና ምእመናን ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙኅን የተገለጸ ሲሆን እስካሁን የተደረገው ድጋፍ ከደረሰው ጉዳት አንጻር ዝቅተኛ በመሆኑ ድጋፉ ላይ ምእመናን ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡ Read more

በአሜሪካ ማእከል የካሮላይና ግንኙነት ጣቢያ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን አስመረቀ

በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል ካሮላይና ግንኙነት ጣቢያ የሚገኘው የአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ለሁለት ወራት የክረምት ትምህርት ያስተማራቸውን ሰባ ስድስት (፸፮) ተማሪዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት በመስጠት የክረምቱን መርሃ ግብር ነሐሴ ፲፱ ቀን ፳፻፲ ዓም አጠናቋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በሻርለት ኖርዝ ካሮላይና የመካነ ብርሃን ቅድሥት ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መሪጌታ ሰናይ ተገኝተው ሕጻናቱንና አዳጊ ወጣቶችን ባርከው አበረታትተዋቸዋል። በዚህ የክረምት ትምህርት መርሃ ግብር ላይ ተጋባዥ እንግዶችና የተመራቂ ሕጻናቱና አዳጊ ወጣቶቹ ቤተሰቦች የተገኙ ሲሆን በአጠቃላይ በክረምቱ መርሃ ግብር ላይ የወላጆች ሱታፌ የላቀ እንደነበር የትምህርትና ሥልጠና ማዕከሉ አስተባባሪዎች ገልጠዋል።
ማዕከሉ በሚቀጥለው ዙር የሚያስተምራቸውንም ተማሪዎች መመዝገቡን ከአስተባባሪዎቹ ለመረዳት ተችሏል።

የአሜሪካ ማዕከል አዲስ ድረገጽ ለቀቀ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል በማኅበሩ በስራ ላይ የዋለውን የድረገጽ ወጥነት አሰራር የጠበቀ አዲስ ድረገጽ ለቋል። በዚህ ድረገጽ ማዕከሉን የሚመለከቱ የተለያዩ ይዘቶች ይለጠፉበታል።