ራስን እንዴት መከላከል ይቻላል?
ራስን እንዴት መከላከል ይቻላል ?
ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ራስን እና ሌሎችን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚችሉ ርምጃዎች አሉ። .
- በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ 2019 (ኮቪድ 19)ን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት የለም።
- በዚህ ህመም ከመያዝ ለመዳን ያለው ተመራጭ መንገድ ራስን ከቫይረሱ ተጋላጭነት ማራቅ ነው።
እጅን ቶሎ ቶሎ መታጠብ
- በተለይም ብዙ ሰው በሚገኝበት አካባቢ ሲሆኑ፣ ከተናፈጡ፣ ካሳልዎት ወይም ካስነጠሱ በኋላ እጅን ቶሎ ቶሎ በሳሙናና በውሃ ሙልጭ አድርጎ ቢያንስ ለ20 ሰከንድ ያህል መታጠብ
- ውሃና ሳሙና በቅርበት ካላገኙ ቢያንስ 60% የአልኮል ይዘት ባለው የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር መጠቀም ይቻላል። ሳኒታይዘር ሲጠቀሙ እጅዎን ከላይም ከታችም ሙሉ ለሙሉ ከቀቡ በኋላ እስኪደርቅ ድረስ አንዱን በአንዱ እጅ እያደረጉ ድረስ ማሸት ።
- አፍን፣ አፍንጫንና ዐይንን ባልታጠበ እጅ መነካካትን ማስወገድ። .
አካላዊ ቅርርብን ማስወገድ
- በቫይረሱ ከተጠቁ ሰዎች ጋር የሚኖርን አካላዊ ቅርርብ ማስወገድ።
- በአካባቢው የኮቪድ 19 ቫይረስ መሰራጨቱ ከተነገረ በኋል ከሰዎች ጋር የሚመከረውን አካላዊ ርቀት መጠበቅ። ይህ በተለይ በቫይረሱ በከባድ ሁኔታ ሊታመሙ የሚችሉ ሰዎችን በቫይረሱ እንዳይጠቁ ለመከላከል ተመራጩ መንገድ ነው። .