ራስን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ራስን እንዴት መከላከል ይቻላል ?

ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ  ራስን እና ሌሎችን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚችሉ ርምጃዎች አሉ። .

  • በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ 2019 (ኮቪድ 19)ን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት የለም።
  • በዚህ ህመም ከመያዝ ለመዳን ያለው ተመራጭ መንገድ ራስን ከቫይረሱ ተጋላጭነት ማራቅ ነው።

 

እጅን ቶሎ ቶሎ መታጠብ

  • በተለይም ብዙ ሰው በሚገኝበት አካባቢ ሲሆኑ፣ ከተናፈጡ፣ ካሳልዎት ወይም ካስነጠሱ በኋላ  እጅን ቶሎ ቶሎ በሳሙናና በውሃ ሙልጭ አድርጎ ቢያንስ ለ20 ሰከንድ ያህል መታጠብ
  • ውሃና ሳሙና በቅርበት ካላገኙ ቢያንስ 60% የአልኮል ይዘት ባለው የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር መጠቀም ይቻላል። ሳኒታይዘር ሲጠቀሙ እጅዎን ከላይም ከታችም ሙሉ ለሙሉ ከቀቡ በኋላ እስኪደርቅ ድረስ አንዱን በአንዱ እጅ እያደረጉ ድረስ ማሸት ።
  • አፍን፣ አፍንጫንና ዐይንን ባልታጠበ እጅ መነካካትን ማስወገድ። .

አካላዊ ቅርርብን ማስወገድ

  • በቫይረሱ ከተጠቁ ሰዎች ጋር የሚኖርን አካላዊ ቅርርብ ማስወገድ።
  • በአካባቢው የኮቪድ 19 ቫይረስ መሰራጨቱ ከተነገረ በኋል ከሰዎች ጋር የሚመከረውን አካላዊ ርቀት መጠበቅ። ይህ በተለይ በቫይረሱ በከባድ ሁኔታ ሊታመሙ የሚችሉ ሰዎችን በቫይረሱ እንዳይጠቁ ለመከላከል ተመራጩ መንገድ ነው። .