የምርምር ዕቅድ /ጥናታዊ ጽሑፍ ጥሪ (Call for Research Proposal/Paper)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አርእስተ ጉዳዮች ላይ በግልም ሆነ በቡድን ጥናት ማድረግ ለሚፈልጉ ተመራማሪዎች የምርምር እቅድ (proposal) ወይም የተጠናቀቁ ጥናታዊ ጽሑፎች ማቅረብ ለሚፈልጉ ጥሪውን ያስተላልፋል።
የምርመር ጭብጦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፣
፩. በቤተክርስቲያን ላይ ለተሳሳቱ ትርክቶች መልስ መስጠት የሚችል ጥናት ማድረግ
፪. የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ምዕመናን የትሩፋት (ፈቃድ) መንፈሳዊ አገልግሎት መርሆዎችና ተግዳሮቶች፣
፫. የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ምዕመናን የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና ተግዳሮቶች፣
፬. የኢትዮጵያውያን ቁጥርና ስብጥር (Demography of Ethiopian Community) በአሜሪካ
የሕዝብ ብዛት፣ ስርጭት በስቴቶች፣ ትዉልድ (፩ኛ፣ ፪ኛ ወ.ዘ.ተ) እና እምነት (ቀድሞ የተሰበሰቡ ምንጮችን /Secondary data) በመጠቀም)፣
፭. የአኅት አብያተ ክርስቲያናት አስተዳደራዊና ተቋማዊ ልምዶች ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በአሜሪካ፣
፮. የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ሕጋዊ መብቶች በኢትዮጵያና ውጭ ሀገራት፣
፯. የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ሐዋርያዊ ተልዕኮና ተደራሽነት በአሜሪካ፣
፰. በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል የሰውሃብት አቅም ከአገልግሎት ተደራሽነት አንጻር፡፡
የመረጡትን ርዕስ የማሳወቂያ ጊዜ፡-እስከ ሕዳር 30, 2013 ዓ.ም (December 9, 2020)
ኢ-ሜል ፡ us.research@eotcmk.org ስልክ ፡ 1 (240) 354-6963; 1(352) 870-6128
በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል ጥናትና ምርምር ክፍል