የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች

ምልክቶች

እስካሁን የተረጋገጡ  የኮረናቫይረስ 2019 (ኮቪድ 19) በሽታ ክስተቶችን ተከትሎ  ቀለል ካሉ  የህመም ምልክቶች እስከ ጽኑ ህመም ሲከፋም እስከሞት የደረሱ የህመም ደርጃዎችና ውጤቶች  ተመዝግበዋል።

እነዚህ ምልክቶች ለቫይረሱ ከተጋለጡ ከ2-14 ቀን (ከሌላ ይህን መሰል ቫይረስ የመቀፍቀፊያ ጊዜ በመነሳት ) ባለው ጊዜ ሊስተዋሉ ይችላሉ።

 

        

ትኩሳት                                ሳል                        የትንፋሽ ማጠር

 

የህክምና ክትትል መሻት የሚያስፈልግበት ጊዜ

የኮቪድ 19 አስቸኳይ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች በሚታዩበት ጊዜ ወዲያውኑ የህኪም ክትትል መሻት ይገባል። አስቸኳይ የማስተንቀቂያ ምልክቶች ዝርዝር  የሚክተተሉትን ያካትታል*

 • ለመተንፈስ መቸገር
 • የማያቋርጥ የደረት ሀመም ወይም ግፊት
 • አዲስ አይነት ብዥታ(ግራ መጋባት ) ወይም ከመኝታ ለመንቃት መቸገር
 • የፊት ወይም የከንፈር ቀለም ወደ ሰማያዊ ቀለም መቀየር

*ይህ ዝርዝር ሁሉንም ምልክቶች ያካተተ አይደለም። እባክዎን ከዚህ የተለየ ጽኑ ወይም አሳሳቢ የሆኑ ምልክቶችን ካዩ ሀኪምዎን ያማክሩ።

ለጽኑ ህመም የመጋለጥ ከፍተኛ እድል ያላቸው ሰዎች

ኮቪድ  19 አዲስ በሽታ በመሆኑ ለጽኑ ህመም የሚዳርጉ የተጋላጭነት ምክንያቶችን በተመለከተ ያለው መረጃ ውሱን ነው። እስካሁን ባለው መረጃ በኮቪድ 19 የተነሳ ለጽኑ ህመም የመጋለጥ ከፍተኛ እድል ካላቸው ውስጥ

 • ዕድሜያቸው 65 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ፥
 • በአረጋውያን መጦሪያ ወይም የረዥም ጊዜ ማገገሚያ ተቋማት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆኑ
 • ሌሎች ከፍተኛ ተጋላጭነት ካላቸው መካከል
  • ከባድ የሆን የሳንባ በሽታ ወይም መለስተኛ አና ጽኑ የአስም በሽታ ያለባቸው ሰዎች
  • ከፍተኛ የሆነ የልብ ችግር ያለባቸው
  • ካንሰርን በመሳሰሉ ህመሞች የተነሳ በሽታ የመቋቋም አቅማቸው የተዳከመ
  • በማንኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ መጠን ያለፈ ክብደት (BMI >= 40) ያላቸው ወይም ከፍ ያለና ተገቢው  ቁጥጥር  ያልተደረገበት እንደ  የስኳር፣ የኩላሊት እና ጉበት በሽታ  ያለባቸው ሰዎችም ከፍ ያለ የተጋላጭነት ዕድል አላቸው።

ለካንሰር የሜሰጥ ህክምና፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የመቅኒ ወይም ሌላ የሰውነት ብልት ንቅለ ተከላ፣ ተገቢው ክትትል ያልተደረገለት ኤችአይቪ/ ኤድስ፣  ረዘም ላለ ጊዜ corticosteroids ወይም ሊሎች የሰውነትን በሽታ የመቋቋም አቅም የሚቀንሱ መድሃኒቶችን መውሰድ እና ሌሎች ብዙ ምክንያቶች የሰውን በሽታ የመቋቋም አቅም ሊጎዱ ይችላሉ። ከመተንፈሻ አካል በሚወጡ ጥቃቅን ጠብታዎች አማካኝነት። እነዚህ ጥቃቅን ጠብታዎች በቅርበት ባሉ ሰዎች አፍና አፍንጫ አልፈው ወደ ሳንባ ሊሳቡ ይችላሉ።

አንድ ሰው ሳይታመም በሽታውን ሊያስተላልፍ ይችላል?

በኮቪድ19 ክፉኛ የተጠቁ ሰዎች ቫይረሱን  በከፍተኛ  ሁኔታ እንደሚአያስተላልፉ ይታሰባል። ነገር ግን በዚህ በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት የበሽታውን ምልክት ሳያሳዩ ለሌሎች ያስተላለፉባቸው አጋጣሚዎች መከሰታቸው ተዘግቧል፤ ነገር ግን ዋነኛ የቫይረሱ መተላለፊያ መንገድ ግን አይደለም። .

በሽታው በቫይረሱ የተበከሉ እቃዎችን እና ቦታዎችን በመንካት ሊተላለፍ ይችላል።

አንድ ሰው በኮቪድ 19 ቫይረስ የተበከለ እቃ ወይም ቦታ በእጁ ከነካ በኋላ  አፉን ፣ አፍንጫውን ወይም ዐይኑን በመንካት በበሽታው ሊያዝ ይችላል፣ ነገር ግን ይህም ዋነኛው የቫይረሱ መተላለፊያ መንገድ ነው ተብሎ አይታሰብም።